Thursday, 2 April 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በደህንነቶች የአሜሪካ ጉዟቸው ታገደ፣ ሻንጣቸው ግን ወደ አሜሪካ ተጉዟል

Eng. Yilkal Getnet, Chairman of the Blue Partyህጋዊ የጉዞ ሠንድ በአግብቡ እንደተሟላ አየር መንገዱ አረጋጧል፡፡ ይሁን እንጂ የወያኔ እንባ ጠበቃ ነጭ ለባሾች አማካኝነት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአገር እንዳይወጣ ተከልክሏል፡፡ የሰጡትም ምንም ዓይነት ሕጋዊ ምክንያት የለም፤ ያሉት ነገር ቢኖር “እርሶዎ ከአገር እንዳይወጡ ትእዛዝ ተሰጥቶናል፣ ነገ ጠዋት 2፡30 ኢሚግሬሽን ይምጡ!” ከማለት በስተቀር፡፡ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ አይነቱ የውንብድና ተግባር ሲፈፀምባቸው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

ኢ/ር ይልቃል ለጉዞ ያዘጋጁት ሻንጣ አስፈላጊው ፍተሻ ከተደረገ በኋላ አውሮፕላን ላይ የተጫነ ሲሆን፣ የሻንጣው ባለቤት የሆኑት ኢ/ር ይልቃል ወደ አሜሪካ መጓዝ ተከልክለው ሻንጣቸው ብቻ ከአገር እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ገዥው መንግስት ከቦታ ወደ ቦታ የመዘዋወር አለም አቀፍ እንዲሁም ህገመንግስታዊ መብት ፣ ያለምንም ሕጋዊ መክንያት መገደቡ የወያኔ መንግሰትን አምባገነንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሣይ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ውንብድና የያዝነውን ትግል የበለጠ አጠንክረን እንድንቀጥል ተጨማሪ ሃይል እንደመሆኑ መጠን በትግላችን የምናመጣውን ውጤት ያፋጥናል፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

Tuesday, 31 March 2015

ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ተፈተው እንደገና ዛሬ ታስረው ሞጆ ላይ ተለቀቁ


አቶ በቀለ ገርባ የ እስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መፈታታቸው ተሰማ::  አቶ በቀለ ዛሬ ተፈተው እቤታቸው ከገቡ በኋላም እንደገና ደህንነቶች “ያልተጣራ ነገር” አለ ብለው እንደገና ወስደው ለሰዓታት ካሰሯቸው በኋላ መልሰው ሞጆ ላይ ለቀዋቸዋል::

የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ “የአቶ በቀለ አፈታት ድራማ” በሚል በዘገበው ዘገባው ላይ የሚከተለውን ጽፏል::

*ዛሬ መጋቢት 21 2007 ዓም አቶ በቀለ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚፈቱበት ቀን ነው።
*ጠዋት ላይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀናን ጨምሮ የአቶ በቀለ መፈታትን ለማየት ወደ ዝዋይ እስር ቤት አቀኑ
*አቶ በቀለ ተፈቱ:: ቤተሰባቸውን በእቅፋቸው አድርገው በደስታ እንባ ታጅበው መነፋፈቃቸውን ገለጹ። ከዚያ ጉዞ ወደ ቤት…
*በድንገት የህወሓት ፖሊሶች ወደ አቶ በቀለ መጡና “መጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይወሰዳሉ” አሉ::   ቤተሰብም አቶ በቀለም ቀልባቸው ተገፈፈ:: ደስታቸው ብን ብሎ ጠፋ!
*በደንጋጤ የተዋጡት ወይዘሮ ሀና ይህንን ጉዳይ ለኦፌኮ አመራሮች አሳወቁ። የኦፌኮ አመራሮች በፍጥነት አቶ በቀለ ይሄዳሉ ወደተባሉበት ቃሊቲ እስር ቤት ተጓዙ።
*ሆኖም ቢጠበቅ-ቢጠበቅ አቶ በቀለ ብቅ ሳይሉ ቀሩ
*አቶ በቀለን ይዘው የነበሩት ጠባቂዎች ታሳሪውን ይዘው ሞጆ አካባቢ ለቀቋቸው።

ውዥንብሩ ለምን እንደተፈጠረ ባይታወቅም ዋናው ደስታው ነውናን ቤተሰባቸው አቶ በቀለ ገርባን ይዞ ወደ አዳማ ናዝሬት ይዞ ሄደ። አቶ በቀለና ሴት ልጃቸው ቦንቱን ኢሳት በስልክ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል::

በካንጋሮው የሕወሓት ፍርድ ቤት “በሽብርተኝነት” ክስ ጥፋተኛ ተብለው 3 ዓመት ከ7 ወር የተፈረደባቸው አቶ በቀለ በመጀመሪያ ስምንት ዓመት ቢፈረድባቸውም ተከራክረው ወደ 5 ዓመት ማስደረጋቸው ይታወቃል:: በየኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ በኣመክሮ መለቀቅ የነበረባቸው ቢሆንም መከልከላቸው ይታወሳል:: እስር ቤትም ህክምናም ሳያገኙ ብዙ ተሰቃይተዋል:: አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር::

Monday, 30 March 2015

U.S. Students Feature Ethiopia’s Reeyot Alemu in ‘Press Uncuffed’ Campaign



Reeyot Alemu is one in a number of journalists who have been prosecuted under the vaguely worded and broad-reaching anti-terrorism laws passed by the Ethiopian legislature in 2009.



Students from the University of Maryland’s Philip Merrill College of Journalism and their professor — Pulitzer Prize-winning Washington Post reporter Dana Priest — have launched the Press Uncuffed campaign to raise awareness about journalists imprisoned around the world.

The campaign, which kicked off last week at the Newseum in Washington, D.C, is being conducted in partnership with the Committee to Protect Journalists (CPJ). It features jailed reporters from nine countries, including Ethiopian Reeyot Alemu, winner of the 2013 UNESCO/Guillermo Cano World Press Freedom Prize. Reeyot is currently serving a 5-year prison term under Ethiopia’s controversial terrorism law.

“These journalists were imprisoned for doing their jobs by governments fearful of a free press,” said CPJ Advocacy Director Courtney Radsch in a statement. “By recognizing these nine intrepid journalists-most of whom were jailed on anti-state or retaliatory charges-we hope to increase public pressure for their release and draw attention to the hundreds of others who have been silenced by their governments.”

CPJ added: “The journalists featured in the campaign have been imprisoned on anti-state or retaliatory charges. Two are being held without charge.”

They are: Ilham Tohti (China), Bheki Makhubu (Swaziland), Reeyot Alemu (Ethiopia), Khadija Ismayilova (Azerbaijan), Jason Rezaian (Iran), Yusuf Ruzimuradov (Uzbekistan), Mahmoud Abou Zeid Shawkan (Egypt), Ta Phong Tan (Vietnam) and Ammar Abdulrasool, (Bahrain).

Friday, 27 March 2015

ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት ህወሓትን ከዱ



የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሎ አበባ ገ/ህይወት፣ ኢህአዴግን መክዳታቸው ተሰማ። ወ/ሎ አበባ ኢህአዴግን የከዱት በቅርቡ ለስብሰባ በሄዱባት ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መሆኑ ታውቋል።

ወደ ሀገራቸው እንደማይመለሱና እዛው አሜሪካ ጥገኝነት እንደሚጠይቁ ቅርባቸው ለሆኑ ሰዎች እንደተናገሩ የሚነገርላቸው ወ/ሎ አበባ ገ/ህይወት፤ ከድርጅት ጉዳይ ኃላፊነታቸው በተጨማሪ በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች ላይ ኃላፊ እንደነበሩ ታውቋል። ግለሰብዋ ተደራራቢ ኃላፊነት የያዙት ከምርጫ ዘጠና ሰባት ወዲህ እንደሆነ ይነገራል።

የህወሓት የበላይነት ባንሰራፋበት በአሁኑ ጊዜ የተባሉትን ብቻ የሚያደርጉና ትዕዛዝ ፈጻሚ ባለሥልጣናት የሎሌነት ሾል እየዋለ ሲያድር እያንገፈገፋቸው ስለሚሄድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እራሳቸውን ለማውጣት አቆብቁበው እንደሚገኙ የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ። በአገር ውስጥ ያሉትና የመሰደድ ዕድል ያላገኙት የህወሓት ተፅዕኖ ያንገፈገፋቸው ባለሥልጣናትም ቢሆኑ የሥርዓቱን አስከፊነት የሚያመላክቱ መረጃዎችን ራሳቸውን በመደበቅ ይፋ እያወጡ እንደሆነ እነዚሁ የፖለቲካ ታዛቢዎች ጠቁመዋል።

ምርጫ በኢትዮጵያ – ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ ክርክር ታገደ

• ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በኢብኮ ስቲዲዮ ከሚደረግው ቀረጻ ተባረዋል

(ነገረ-ኢትዮጵያ) ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ መጋቢት 18/2007 ዓ.ም ምሽት ኢብኮ (EBC) ላይ ከሚቀርበው የ‹‹áŒá‰Ľáˆ­áŠ“ እና ገጠር ልማት›› ላይ ሊያደርገው የነበረው የምርጫ ክርክር ላይ እንዳይቀርብ መታገዱን የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ለቀረጻ ወደ ኢብኮ ስቲድዮ ባቀኑበት ወቅት የድርጅቱ ምክትል ሾል አስካሄጅ አቶ ተሻለ ‹‹á‰Łáˆˆáˆá‹ ያላሰባችሁትን የምርጫ ክርክር እድል ሰጥተናችኋል፡፡ በመሆኑም ዛሬ መከራከር አትችሉም›› ተብለው መባረራቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሰአብአዊ መብት ዙሪያ ኢብኮ ላይ በቀረው የምርጫ ክርክር ላይ አንድ ፓርቲ ለመቅረብ ፈቃደኛ አለመሆኑን በመገልጹ በክርክር 5 ፓርቲዎች እንዲቀርቡ የሚደረግ በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ዛሬ ምሽት በግብርና እና ገጠር ልማት ላይ የሚደረገው ክርክር ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ዕጣ የደረሰውና የፀደቀ ፕሮግራም ነው፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ከቀረጻ ተባርሬያለሁ ያሉት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹áŠ˘á‰ĽáŠŽ በፕሮግራም የተያዘ የምርጫ ክርክር ላይ እንዳንቀርብ ያደረገው እሁድ በ15 ከተሞች ሰልፎች እንዳለን ስለለሚያውቅና የዛሬው ክርክር በየአካባቢው ያለውን ህዝብ እንዳያነቃቃ ተፈልጎ ነው›› ብለዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አክለውም ‹‹áŠĽáˆľáŠŤáˆáŠ• እየተደረጉት ባሉት ክርክሮች ሰማያዊ የኢህአዴግን ተግባራት እያጋለጠና ጠንካራ አማራጮችን እያቀረበ በመሆኑ ነው፡፡ ስለሆነም ኢብኮ ኢህአዴግን አግዞ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ እያደረገ ነው›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

Wednesday, 25 March 2015

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ


• ኢብኮና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት መልሰዋል
• ‹‹áŠ áˆ›áˆŤáŒŤá‰˝áŠ• እንዳናቀርብ እየተከለከልን ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹áŠ áŠ“áˆľá‰°áˆ‹áˆááˆ›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹áˆ˜áŠ•áŒáˆľá‰łá‹Š አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹á‰ á‰°áˆˆá‹Ťá‹Š ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹á‹¨áˆ…á‹ˆáˆ“á‰ľ/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹á‹¨áˆ…á‹ˆáˆ“á‰ľ/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹áŠĽáŠ› ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹áŠ¨áˆ€áŒˆáˆŞá‰ą ሰንደቅ አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለሾ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

Tuesday, 24 March 2015

የጦማርያንና ጋዜጠኞቹ አቤቱታዎች ውድቅ ተደረጉ


በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሦስቱ ወዳጅ ጋዜጠኞች መጋቢት 15/2007 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡

መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች ባቀረቧቸው ሁለት አቤቱታዎች ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህም አንደኛ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ካለው ማስረጃ ዝርዝር ውስጥ 12 የኦዲዮ-ቪዲዮ ሲዲዎች አያይዞ ያቀረበ ቢሆንም፣ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች እስካሁን ባለመድረሳቸው ተከሳሾች የቀረበባቸውን ማስረጃ ተመልክተው መልስ ለማዘጋጀት ሲዲዎቹ እንዲሰጧቸው ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ 4ኛ ተከሳሽ ማህሌት ፋንታሁን እና 9ኛ ተከሳሽ ኤዶም ካሳዬ በቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ ከጎብኝዎቻቸው መከልከል ጋር በተያያዘ አቅርበውት በነበረው አቤቱታ ላይ ብይን መስጠት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም ሁለቱንም አቤቱታዎች ውድቅ አድርጓል፡፡

የሲዲ ማስረጃውን በተመለከተ አቃቤ ህግ ማስረጃዎችን ኢግዚቪት ብሎ ስላስመዘገበ አሁን በዚህ ደረጃ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች የሚደርሱበት አግባብ የለም በሚል ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን አቤቱታ እንዳልተቀበለው ገልጹዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ማስረጃ በመስማት ሂደት ወቅት ማስረጃዎችን እየተመለከቱ መልስ እንዲሰጡ እንጂ ቀድሞ እጃቸው የሚደርስበት አሰራር የለም ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡


ፍርድ ቤቱ የቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ በሁለቱ ሴት ተከሳሾች የቀረበውን አቤቱታም ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በተከሳሾች የቀረበውን አቤቱታ እና የእስር ቤቱ አስተዳደር የሰጠውን መልስ መመልከቱን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ ‹‹áˆˆá‰€áˆ¨á‰ á‹ አቤቱታ ማስረጃ ተያይዞ ያልቀረበ በመሆኑ…›› በሚል አቤቱታውን ቅድቅ አድርጓል፡፡ ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ከሰኞ መጋቢት 21/2007 ጀምሮ ለሦሰት ቀናት ይሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡