Wednesday, 6 July 2016

የአዲስ አበባ መስተዳድር ዜጎችን የማፈናቀሉን እርምጃ እንዲያቆም የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ጠየቀ

የአዲስ አበባ መስተዳድር ዜጎችን የማፈናቀሉን እርምጃ እንዲያቆም የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ጠየቀ

አብዛሃኞቹ ዜጎች ካርታ ባይኖራቸውም ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸውንና የመብራትና ውሃን የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ሲያገኙ እንደነበር ሰመጉ ገልጿል።

“እነዚህ ዜጎች አስቀድሞ ሕጋዊነትን በያዘ መልኩ መኖሪያዎችን እንዲሰሩ መደረግ ነበረበት። ይህ ከሆነ በኋላ ሕገወጥ ናችሁ በማለት አፍራሽ ግብረኃይል አሰማርቶ በክረምት ነዋሪዎች ላይ ቤት ማፍረስ ኢሰብዓዊ ነው” ሲል ሰመጉ ድርጊቱን በጽኑ ኮንኗል። በ አፍራሽ ግብረኃይሉ ቤቶቻቸው በክረምት ወራት የፈረሰባቸው ዜጎች ቁጥራቸው ከአስር ሽህ እንደሚበልጥና ታዳጊ ሕጻናትና አዛውንት ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ጠቅሷል።

ሰመጉ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ፣ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ሕገ መንግሥቱንና ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የፈረመቻቸውን የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ስምምነቶች በተለይም የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንን በግልጽ የሚጻረር ነው ብሎአል።


ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በደላቸውን በወኪሎቻቸው አማካኝነት ለሰመጉ አሰምተዋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ወረገኑ በሚባል ቦታ ላይ ለበርካታ ዓመታት ቤት ሠርተው፣ ትዳር መሥርተው የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው ቆርቆሮ፣ በርና መስኮታቸው እየተነቃቀለ በአፍራሽ ግብረ ኃይል መወሰዱን ተጎጂዎቹ ማስረዳታቸውንና ሰመጉም ባለሙያዎችን ልኮ ጉዳዩን በአካል በመገኘት ማረጋገጡን አስታውቋል። በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀጣና 01 መንደር 06 በተለምዶ አጠራር ቀርሳና ኮንቶማ ቁጥራቸው ከ9 ሽህ 617 በላይ አባወራዎች በጠቅላላ 19 ሽህ 624 ነዋሪዎች ከ10 እስከ 15 ዓመት ከኖሩበት ቦታ፣ ‹‹ሕጋዊ አይደላችሁም ቦታው ለቄራ አገልግሎት ስለሚፈለግ ልቀቁ›› እንደተባሉ ሰመጉ ሪፖርት እንደደረሰው ጠቅሷል።


በግጭቱ ለዜጎች ሕይወት መጥፋት፣ አካል መጉደልና ንብረት መውደም ተጠያቂ የሆኑ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ የዜጎች መፈናቀል እንዲያቆም፣ ጉዳዩ በጥንቃቄ ተጠንቶ ካሳ ለሚገባቸው ሁሉ ካሳ እንዲከፈልና ቤታቸው ለፈረሰባቸውና በየቦታው ተበትነው ለሚገኙ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ሁሉ ሕጋዊ፣ ሰብዓዊና ቁሳዊ እገዛ፣ እንዲሁም መፍትሔ እንዲሰጧቸው ድርጅቱ ጠይቋል።


 





Exiled prominent journalist, activist wrote open letter to Ethiopia’s security chief

Exiled prominent journalist, activist wrote open letter to Ethiopia’s security chief following threats to their family back home by security operatives

Exiled journalist Sisay Agena and Tamagn Beyene, an activist and a well-known critic of the Ethiopian government wrote an open letter to the country’s security chief, Getachew Asefa following intimidation against their family back home in order to silence their criticism of the government.
In a joint letter released on Tuesday, Sisay and Tamagn, who now live in exile in the United States, wrote that agents of the regime and operatives of the Security and Intelligence Service paid a visit to their respective families on June 29, 2016, and offered briberies and intimidations in what they called “an attempt to stop us from our efforts to bring freedom to our country.”

“We are well aware that our everyday effort to realize our dream of having a free country would not be welcomed by the powers that be in Ethiopia; but we have never expected that your intelligence and security operatives would pay a visit to our family back home to threaten them or offer enticements so we would stop our struggle,” said the joint letter.

Sisay, managing editor at ESAT and producer of several programs, is known for his sharp criticism of the tyrannical regime back in his country, which is known to be one of the World’s top jailers of journalists. He was in and out of jail for several years before he was finally forced into exile.
A former comedian known for his wit and a man who once dominated the stages of theaters in his homeland, Tamagn Beyene left his country two decades ago. But having seen the sufferings of his fellow Ethiopians at the hands of tyrants, he decided to use his influence and skills to be a voice to the voiceless. He also runs a weekly talk show at ESAT.

“Threats against our families, holding them hostages and presenting enticements would not in any way stop us from our struggle for freedom,” their joint letter said in conclusion.

Tuesday, 5 July 2016

Security forces detain hundreds protesting home demolition

Security forces have detained over 200 people in the capital Addis Ababa after thousands of homes, deemed illegal by the government, were demolished.

Six people, including two police officers, were killed in the confrontation last week and authorities are carrying out mass arrests in connection with the killings of the officers. The residents said the regime was indiscriminately arresting citizens who had nothing to do with the killing of the officers. Reports also said over 40 police officers, who sustained injuries in clashes with residents, have been admitted to the hospital.

Some residents told local media that not only their houses were torn down but security forces have beaten and harassed them.

Of the over 30,000 houses built in the area, authorities plan to demolish most of them that were deemed illegal. There are also plans by the city administration to carry out further demolition of houses in other areas of the capital.




ከኦሮሚያ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ዜጎች ቁጥር 50ሺህ እንደሚደርስ ዶ/ር መረራ አስታወቁ

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከመንፈቅ በላይ የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ወደ እስር ቤት የተጋዙ ዜጎች ቁጥር ከ40ሺህ እስከ 50ሺህ እንደሚገመት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ። ወጣቶቹ በስርዓቱ ላይ ተቃውሟቸውን ከሚገልጹባቸው መንገዶች አንዱ ባለስልጣናት ስርዓቱን እንዲያወግዙና መንገድ በድንጋይ እንዲዘጉ ማስገደድ እንደነበርም አመልክተዋል። ኦህዴድ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ መስከረም ወር ላይ ስራ ጀምሮ፣ በህዳር ወር የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ስለምርጫው ውጤት በራሱ የሚናገረው ነገር መኖሩን ያመለከቱት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ምዕራብያውያኑ በምርጫው ከ50 እስከ 60 ወንበር ለተቃዋሚዎች ይለቀቃል የሚል ዕምነት እንደነበራቸውም አስታወሰዋል። 

ምርጫው በኢህአዴግ አሸናፊነት ተጠናቀቀ በተባለ ማግስት ኦሮሚያ ክልል ግንጪ ውስጥ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከህጻናት እስከ አዛውንት ሌላው ቀርቶ የአካባቢው ሚሊሺያዎችን ጭምር ያሳተፈ እንደነበር ገልጸዋል። ወሊሶ አካባቢ በአንድ ባለስልጣን ላይ ወጣቶች የፈጸሙትንና በማስገደድ መንገድ ያዘጉበትንም ሁኔታ ዶ/ር መረራ ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ወሊሶ ላይ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሃላፊ ወጣቶች ሲመጡባቸው ጠረጴዛ ስር ለመደበቅ ያደረጉትን ሙከራ በኋላም አስገድደዋቸው ድንጋይ እየተሸከሙ መንገድ መዝጋታቸውን በዚሁ ቃለምልልስ አስታውሰዋል። በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ በተቀጣጠለበት ወቅት የሃገሪቱ የደህንነት ሃላፊዎች የመድረክ አባል ፓርቲዎችን ከኦፌኮ ነጥለው በማነጋገር ስብስቡን ለመከፋፈል መሞከራቸውንም አስታውቀዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ተገደው መውጣታቸውን የገለጹት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት የነበሩት እንድርያስ እሸቴ ከየትኛውም ተቋም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሳይሰጣቸው ፕሮፌሰር እየተባሉ ሲጠሩ መቆየታቸውን በዚሁ ቃለምልልስ “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎችና አልታረቅ ያሉ ህልሞች” በሚለው መጽሃፋቸው በዝርዝር ተመልክተዋል።

 ኢሳት

Sunday, 3 July 2016

Journalist Reeyot Alemu roasted TPLF agent Gebrekiros Abraha

A few weeks ago Ethiopians from all walks of life gathered in Nashville, Tennessee, to support ESAT and discuss issues of concern. Reeyot Alemu known for her courage and unwavering stand against tyranny was a guest of honor. Gross human rights violations was top on the agenda.

The inconvenient truth was too uncomfortable for a TPLF spy who sneaked in the meeting hall. The TPLF agent, who even worked at the spying entity called Information Network Security Agency, was full of himself. Gebrekiros Abraha, wanted to lecture and dictate what freedom-loving Ethiopians gathered should and should not do. He told them not to raise money for ESAT. According to him, the only enemy for oppressed Ethiopians was poverty. “You should know your enemy,” he lectured.
“If you don’t know your enemy, weha bewektut enboch” he said with a mix of faltering English and Amharic.

People took turns to vent out their anger at his arrogance and ignorance. But it was Reeyot Alemu who roasted the TPLF agent. “Let alone our money, we will give our blood” she told him.

Watch the full video(Amharic)


Saturday, 2 July 2016

በናይሮቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ አደረጉ

በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሀብታሙ አያሌው እገዳው ተነስቶለት የውጪ ህክምና እንዲያግኝ በናይሮቢ-አምነስቲ ቢሮ ፊትለፊት በረሀብ አድማ ጥያቄ ሲያቀርቡ ዋሉ። ሥርዓቱ በፈጠረባቸው ጫና ለስደት የተዳረጉት እነኚህ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች በቀድመው አንድነት ፓርቲ አመራር በሀብታሙ አያሌው ምስል የተሰራ ቲሸርት በመልበስ ፤በቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር በሀብታሙ አያሌው ላይ የተጣለበት የፍርድ ቤት እግድ እንዲነሳና በውጪ ሀገር ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ የሰብዓዊ መብት ተቋሙ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ሀሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸውና ሙያቸውን ተግባራዊ በማድረጋቸው ሳቢያ በአገዛዙ አለስቃይና እንግልት የተዳረጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ወደ ኬንያ ኡጋንዳና ወደሌሎች የተለያዩ ሀገራት ተሰደው በችግርና በስጋት እንደሚገኙ ይታወቃል። 

በረሀብ አድማ ላይ ሆነው በናይሮቢ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጽህፈት ቤት በመገኘት ጥያቄ ሲያቀርቡ የዋሉት እነኚህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሀብታሙ አያሌው ህይወት ላይ የከፋ አደጋ እንዳይደርስ ያደረባቸውን ስጋት በመግለጽ እንደ ሀብታሙ ሁሉ በተለያዩ እስር ቤቶች እየተገረፉና በህመም እየተሰቃዩ ያሉ የህሊና እስረኞች እንዲለቀቁና ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ተማጽነዋል። ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ትናንት እና ዛሬ ሐብታሙ አያሌው የጉዙ እግዱ ተነስቶለት በውጪ ሀገር ህክምና እንዲያገኝ በዘመቻ መልክ እየጠየቁ ይገኛሉ። 

ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ በዚሁ ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማፘም ደሳለኝ ደብዳቤ እንደጻፈ ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።


Friday, 1 July 2016

በአወዳይ በተነሳው ተቃውሞ ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 4 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት) በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው አስተዳዳሪ በከፈተው ተኩስ  ሁለት ህጻናት እና  አንድ ጎልማሳ ተገድለዋል። ነዋሪዎች ማምሻውን ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የሟቾች ቁጥር 7 ድርሷል።

ኢብራሂም ሙሜ የሚባል ባለ ጸጉር ቤት እና አህመድ አልዬ የሚባል ባለሞባይል ቤት አሊ መሰራ ህንጻ እና አዋሽ ባንክ መሃል የሚገኘው ቤታቸው  ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሌሊት ላይ መቃጠሉን ተከትሎ ህዝቡ ለተጎጂ ቤተሰቦች የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰብ ሲጀምሩ ፖሊሶች ጣልቃ ገብተው ለምን ተሰባሰባችሁ በማለት ተኩስ ከፍተዋል።

የአወዳይ 01 ቀበሌ ሊቀመንበር የሆነው አቶ አብዲ እድሪስ በከፈተው ተኩስ ሁለት ህናጻንት ጨምሮ 3 ሰዎች ተገድልዋል።  ፌደራል ፖሊሶች ደግሞ 4 ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትክክለኛውን የሟቾቾችን ቁጥር ለማወቅ ኢሳት ያደረገው ጥረት አልተሰካም።  በድርጊቱ የተበሳጨው ህዝብ ወደ ሊቀመንበሩ ቤት በማምራት ሁለቱንም መኖሪያ ቤቶቹን ያቃጠለ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩ ወደ ሃረር ሸሽቶ ሲያመልጥ ፌደራል ፖሊሶች ደግሞ ባለቤቱንና ልጆቹን ይዘው ከከተማ አስወጥተዋቸዋል።

ከጅጅጋ እና ሃረር የተነሱ ተሽከርካሪዎች መንገድ ተዘግቶባቸው  ወደ ሃረር የተመለሱ ሲሆን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ባንኮች ተዘግተው ውለዋል። የተሰባበሩ ተሸከርካሪዎች መኖራቸውንም የአይን እማኞች ገልጸዋል። ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩ መምህራን መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ስራ ሳይሄዱ ወደ ሃረር ተመልሰዋል።

የኦሮሞ ወጣቶች ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ወቅት ጀምሮ በአካባቢው የሚታየው ተቃውሞ እስካሁን አልቆመም። ተቃውሞችን ተከትሎ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በግፍ ተገድለዋል። ሂማንራይትስ ወችና ሌሎችም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ግድያው በገለልለተኛ ወገን እንዲጣራ በመጠየቅ ላይ ናቸው።